በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

443

መግቢያ

ኢትዮጵያ ዘመናዊ የፍትህነና የዳኝነት ስርዓት ከመገንባቱ ብዙ ዓመታት አስቀድሞ የተለያዩ ባህላዊና ሀይማታዊ የፍትህ እና የዳኝነት ስርዓትን ስታራምድ ኖራለች፡፡ ይህ የዳኝነት ስርዓት ኢትዮጵያዊ ባህልን፣ ወግን፣ አኗኗርንና እምነትን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ የዳኝነት ስርዓት ሲሆን ስርዓቱን የሚዘውሩት ደግሞ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ነበሩ፡፡ ይህ ስርዓት ዘመናዊ የዳኝነት እና የፍትህ ተቋማት ለመገንባታቸው የራሱን አስተዋፅዖ ያበረከተ ሲሆን በፍትህ አሰጣጥ ደረጃም ለዘመናዊው የዳኝነትና የፍትህ አሰጣጥ ሂደት የራሱን አሻራ አሳርፏል፡፡